የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሠራተኞችና የሥራ ቅጥር ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

March 03, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሠራተኞችና የሥራ ቅጥር ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ቢህ ኢማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ጉባዔ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎን በተፈጠረው መድረክም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሠራተኞች ሥራ፣ የሥራ ቅጥር እና የጉልበት ፍልሠት ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡