የሀገር ውስጥ ዜና

አዋሽ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 30 ሚሊየን ብር ለገሰ

By Mikias Ayele

March 03, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

አዋሽ ባንክ ባለፈው ዓመትም በቦረና እና ጉጂ ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች60 ሚሊየን ብር መለገሱን የባንኩ መረጃ ያመላክታል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም በምዕራብ ኦሮሚያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ዜጎችና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ቤት ለፈረሰባቸዉ አባወራዎችም የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።