Fana: At a Speed of Life!

የሲንቄ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ115 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲንቄ ባንክ በቦረና ዞን በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ115 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ማህበራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ንዋይ መገርሳ፥ ባንኩ ላለፋት 25 አመታት በማይክሮ ፋይናንስነት በገጠር ያለውን የህብረተሰብ ክፍል ሲያገለግል መቆየቱን ተናግረዋል ።

ወደ ባንክነት ካደገ 10 ወራት የተቆጠሩ ሲሆን፥ ከ7 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ይዞ ከ500 በላይ ቅርንጫፎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መክፈት መቻሉንም ነው ያመለከቱት።

ባንኩ በዛሬው እለት ከሰራተኞቹ ያሰባሰበውን 115 ሚሊየን ብር በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እንዲደርስ አስረክቧል።።

ድጋፋን የተረከቡት የቦሳ ጎንፋ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮሚሽነር ሙስጠፋ አድር፥ የተደረገው ድጋፍ የተፈጠረውን ችግር በማቃለል እና እየተደረገ ያለውን የሰውና የእንስሳት ህይወት የመታደግ ስራ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

አሁንም የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚው ጥሪ አቅርበዋል ።

በበረከት ተካልኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.