ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና የነዳጅና ጋዝ ክምችት ማግኘቷን አስታወቀች

By Amele Demsew

March 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ሰፊ የነዳጅና ጋዝ ክምችት ማግኘቷን አስታወቀች።

የሃገሪቱ የነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው ክምችቱ፥ በቦሃይ ባህር በሚገኘው ቦዦንግ 26-6 የነዳጅ ማውጫ ስፍራ የተገኘ ነው።

አሁን ድፍድፍ ነዳጅ የተገኘበት ስፍራ የነዳጅ ክምችት ያለበት ሶስተኛው ስፍራ እንደሆነ መገለጹን አር ቲ ዘግቧል።

በስፍራው 100 ሚሊየን ቶን ቀላል የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት መገኘቱንም ነው ኮርፖሬሽኑ ያስታወቀው።

ድፍድፍ ነዳጁ በተገኘበት ስፍራም አስፈላጊው ቁፋሮ መደረጉንም ኮርፖሬሽኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በስፍራው በተደረገው ሙከራም 2 ሺህ 40 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ እና 11 ነጥብ 45 ሚሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ በቀን ማምረት እንደሚቻል ኮርፖሬሽን ገልጿል።