Fana: At a Speed of Life!

ከ195 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከየካቲት 17 ቀን እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ከ195 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን አስታወቀ።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተያዙ ሲሆን÷ 129 ሚሊየን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 66 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የወጭ፤ በድምሩ ከ195 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ዘጠኝ ግለሰቦች እና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.