የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በአዘርባጃን ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

March 04, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአዘርባጃን ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም አቶ ደመቀ መኮንን÷በኢትዮጵያ  ስላለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችና መንግስት በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩ ለውጭ ባለሃብቶች እያደረገ ስላለው ማበረታቻ ገለጻ አድርገዋል።

ባለሃብቶቹ በበኩላቸው÷ በአዘርባጃን የተለያዩ ካምፓኒዎች እንዳሏቸውና በተለያዩ ዘርፎችም መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ መሆኑን መግለጻቸውን በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን፣በግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት  ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል፡፡