ለገበታ ለትውልድ ጥሪ የተደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ደረሰ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገበታ ለትውልድ ጥሪ እስካሁን የተደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባቀረቡት የገበታ ለትውልድ ጥሪ መሠረት ትናንት ማምሻውን በሀገር ወዳድ ባለሃብቶች እና በእምነት ተቋማት 207 ሚሊየን ብር ቃል ተገብቷል ብለዋል።
ለገበታ ለትውልድ ጥሪ በትናንትናው ዕለት ቃል የተገባውን ገንዘብ ጨምሮ እስካሁን 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ድጋፍ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች “የምትለግስ እንጂ የማትለምን ኢትዮጵያን ለመገንባት በምናደርገው ጥረት ከጎናችን ሆናችሁ ለደገፋችሁን እና ቃል የተገባውን ገቢ እያደረጋችሁ ያላችሁትን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን”ብለዋል።