የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኳታሩ አሚር ሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር ተወያዩ

By Tamrat Bishaw

March 05, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኳታሩ አሚር ሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፣ “ዛሬ ከሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ ጋር በመገናኘታችን ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።

ከአሚሩ ጋር በነበራቸው ውይይትም የሁለትዮሽ ግንኙነትን ጨምሮ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው የገለጹት።

በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ለኳታር ኢንቨስትመንቶች ብዙ ዕድሎች እንዳሉ ማንሳታቸውንም ጠቁመዋል፡፡