ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አል ታኒን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኳታር ግዛት አሚር ሼክ ተሚም ኢብን ሀማድ አልታኒ አባት ሼክ ሃማድ ቢን ካሊፋ አልታኒን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ማህበራዊ ልማትን እና ኢንቨስትመንቶችን በመደገፍ ላይ ያተኮረ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡