በዶ/ር አለሙ ስሜ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የተለያዩ ተቋማትን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የተለያዩ ተቋማትን ጎብኝቷል፡፡
ልዑካኑ ዳመርጆግ ኢንዱስትሪያል ፓርክን እና የናጋድ ጣቢያን መጎብኘታቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ወደብ ፓርክ ፕሮጀክት አካል ሆኖ የተገነባው የነዳጅ ዘይት ተርሚናል ላይ የታየው መሻሻል መገምገሙ ተጠቁሟል፡፡
የየነዳጅ ዘይት ተርሚናሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ሆኖ እንደሚያገለግል ነው የተገለጸው፡፡
ተርሚናሉን ወደ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ለማገናኘት 13 ኪሎ ሜትር ባቡር መንገድ እንደሚገነባም ተመላክቷል፡፡፡