የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

By Melaku Gedif

March 06, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከደቡብ ኮሪያ የዓለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት ዋና ጸሃፊ ሁን ሞክ ሊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአምራች ኢንዱስትሪው  ዘርፍ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፉ በተለይም በጫማ ስራ ላይ የተሰማሩ የኮሪያ ባለሃብቶችን በኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ዘርፉን ሊያነቃቁ የሚችሉ “የማይንድ ሴት” ስልጠናን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ስምምነት ላይ  መድረሳቸው ተጠቁሟል፡፡