Fana: At a Speed of Life!

የዝናብ ውሃን የማጠራቀም ፕሮጀክትን በድርቅ ተጎጂ ለሆኑ አካባቢዎች ለመተግበር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዝናብ ውሃን በማጠራቀም ፕሮጀክት ለድርቅ ተጋለጭ ለሆኑ አካባቢዎች በተግባር ላይ ለማዋል እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ገለጹ።

“ግድቤን በደጄ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሙከራ ደረጃ ፕሮጀክቱ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ተመክቷል፡፡

ከዚህ ተሞክሮ በመነሳትም በድርቅ ተጎጂ በሆነው በቦረና ዞንና በአማራ ክልል ጎንደር ዞን አካባቢዎች የፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

ኢንጂነር ሐብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት÷ “ግድቤን በደጄ” የዝናብ ውሃን የማጠራቀም ፕሮጀክት በቦረና ዞን በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና መንደሮች በመተግበር ላይ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የዝናብ ውሃን በማሰባሰብ በዘመናዊ መንገድ ወደ ተገነባ ገንዳ በማጠራቀም ንጽህናው በተጠበቀ መልኩ በአነስተኛ ማሽን በማውጣት ሕብረተሰቡ እንዲጠቀም ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

ፕሮጀክቱ በቦረና ዞን ስምንት ትምህርት ቤቶችና በአንድ አካባቢ ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው÷ የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.