የሀገር ውስጥ ዜና

የኳታሩ “ኢዱኬሽን አበቭ ኦል” ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የትምህርት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ

By Amele Demsew

March 07, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኳታሩ “ኢዱኬሽን አበቭ ኦል” ፋውንዴሽን እና የፌዴራል መንግሥት በኢትዮጵያ የትምህርት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በትምህርት ጉዳይ ከሚሠራው የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፋሃድ ሃማድ ሀሰን አል-ሱላይቲ ጋር በዶሃ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ፋውንዴሽኑ በግጭት ምክንያት የተጎዱ የትምህርት ተቋማትን መልሶ በመገንባት ውስጥ ሊኖረው ስለሚችለው ሚናም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

“ኢዱኬሽን አበቭ ኦል” ፋውንዴሽን በፈረንጆቹ 2012 የተቋቋመ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው እና ሁሉን አቀፍ የትምህርት ተደራሽነት እንዲኖር የሚሠራ ድርጅት ነው።