Fana: At a Speed of Life!

የኮሌራ በሽታ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሌራ በሽታ ከ20 ዓመታት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የኢኮኖሚ ቀውስ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የኮሮና ቫይረስ ተጽዕኖ በሽታው በፍጥነት እንዲስፋፋ ያደረጉ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በ30 ሀገራት ውስጥ በኮሌራ በሽታ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የውሃ ወለድ በሽታ የሆነው ኮሌራ ስርጭት በዚህ ደረጃ ሲያሻቅብ ከ20 ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ጠቁሟል፡፡

በተለይም በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ሀገራት የጣለው ከባድ ዝናብ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰራጭ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ሶሪያ ከ15 ዓመታት ወዲህ እንዲሁም ሊባኖስ ከ30 ዓመታት ወዲህ በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ያወጁ ሀገራት መሆናቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

የበሽታውን የስርጭት ሁኔታ ለመግታትም ሀገራት ለጤና አጠባበቅ የሚየስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላት እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.