የፓኪስታን የኢንቨስትመንትና የንግድ ልዑክ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክን እየጎበኘ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ70 በላይ የፓኪስታን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑካን ቡድን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክን እየጎበኘ ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ÷ለልዑካን ቡድኑ የፓርኩን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ በሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡
ልዑኩ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚኖረው ቆይታ የተለያዩ አምራች ኩባንያዎችን የምርት ሂደትና የስራ እንቅስቃሴ እንደሚጎበኝ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡