Fana: At a Speed of Life!

በታዳጊ ክልሎች ሲተገበር የቆየው የ37 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የእናቶች ጤና ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ) በታዳጊ ክልሎች ሲተገብር የቆየውን የ37 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የጤና ፕሮጀክቶች ማጠናቀቁን ገለጸ፡፡

ፕሮጀክቶቹን የተተገበሩት በአፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች መሆኑን አስታውሷል፡፡

ዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ መሠረት ፕሮጀክቱ ይፋ የተደረገው በፈረንጆቹ 2017 ላይ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ ለሴቶች የቅድመ ወሊድ ክብካቤ ፣ የጨቅላ ህጻናት ክብካቤ፣ በወሊድ እና ድኅረ ወሊድ ጊዜ በጤና ባለሙያዎች የታገዘ የእናቶች የጤና ክብካቤ እንዲሁም የጤና ክትትል ማድረግ ተችሏል።

ፕሮጀክቱ የተተገበረው “አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ” የተሠኘው የአፍሪካ የሕክምና እና ጥናት ፋውንዴሽን ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር ነው ተብሏል፡፡

በዚህም በአራቱ ክልሎች ያለውን የጤና ተደራሽነት ማሻሻል መቻሉን አመላክቷል፡፡

በታዳጊ ክልሎች 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የሚገመት የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽ ማድረጉንም ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በፕሮጀክቱ 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ይህል ገንዘብ ያልተጠበቁ የተፈጥሮ አደጋዎች በተከሰቱባቸው አካባቢዎች ከጤና ጋር በተገናኘ የኮቪድ 19ን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ነው ያስታወቀው።

ገንዘቡ የድርቅ፣ የጎርፍ አደጋዎችን ጨምሮ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የአደጋ ጊዜ ድጋፍ ለማድረስ መዋሉም ተገልጿል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.