የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 15ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

By Tamrat Bishaw

March 07, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ስምንተኛ የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

ጉባኤው የምክር ቤቱ አባላት አሰራር እና ሥነ-ምግባር ማሻሻያ እንዲሁም የጠበቆች አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል።

ከዚህ ሌላ ምክር ቤቱ በተጓደሉ የሰው ሃብት ልማትና ሌሎችም ቋሚ ኮሚቴዎች ምትክ አንድ ሰብሳቢና አምስት አባላትን በማሟያነት፣ 61 የጠቅላይ፣ የዞን እና የወረዳ ዳኞች ሹመቶችን አፅድቋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አሻድሊ ሃሰን በዕጩነት ያቀረቧቸው አቶ ሰንበታ ቀጄላ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።

በክልሉ የፍትህ አሰጣጥ ሂደት ማጠናከር ይገባል ሲሉ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ አለምነሽ ይባስ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።