ቢዝነስ

ብሮሚን እና ክሮሊን ማዕድናት በቅርቡ ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ ሊቀርቡ ነው

By Alemayehu Geremew

March 07, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሮሚን እና የክሮሊን የማዕድን ምርቶች በቅርቡ ለውጭ እና ለሀገር ውስጥ ገበያ እንደሚውሉ የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቴዎስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት ÷ በአፋር አካባቢ ጨዋማ ባህሪ ያለውን የብሮሚን እና የክሮሊን የማዕድን ምርቶች በተጠናከረ መንገድ የማምረት ሥራ ተጀምሯል፡፡

ምርቶቹን በቅርቡ ለውጭና ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማዋል እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በሌሎች አካባቢዎችም አዳዲስ የማዕድን ሐብቶችን ወደ ምርት ለማስገባት ሚኒስቴሩ በተጠናከረ መንገድ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ጌጣጌጦችን እና አዳዲስ የማዕድናት ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት በሂደት ላይ መሆናቸውን አክለዋል።

በዋናነት ዘርፉን የማዘመን ስራ እየተሠራ እንደሆነም ተጠቁሟል።

በታሪክ አዱኛ