የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ለአዲሱ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Shambel Mihret

March 07, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በቅርቡ በናይጄሪያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቦላ ቲኑቡ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ፥ ምርጫው በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየና ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያገለግላል የሚል እምነት እንዳላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡