የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

March 07, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ተወያዩ ፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ለሥራ ጉብኝት ጅቡቲ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በዚህ የሥራ ጉብኝት ወቅትም ሚኒስትሩ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ተመካክረዋል።

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በትራንስፖርት ዘርፍ በጋራ ሊሠሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩም ነው የተገለጸው።

የዲኪል-ጋላፊ መንገድን ማጠናቀቅ እና ለተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን መፍጠርን አስመልክተውም ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ መነሣቱን በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!