Fana: At a Speed of Life!

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጭ ሐሳቦች ማሰባሰቢያ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጭ ሐሳቦች ማሰባሰቢያ ውይይት ዛሬ መካሄድ ጀመረ፡፡

ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው÷ ከሲቪል ማኅበራት፣ ከመገናኛ ብዙኃን እና የዲሞክራሲ ተቋማት ጋር ነው፡፡

መድረኩ ባለፈው ሰኞ ከተካሄደው ሀገራዊ የፖሊሲ አማራጮች ግብዓት ማሰባሰቢያ ምክክር ማስጀመሪያ ቀጥሎ ሁለተኛው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ካውንስል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሄኖክ መለሰ ባደረጉት ንግግር÷ በግጭት ወቅት በሚደርሱ ጥሰቶች ዋነኛ ሰለባ በሚሆኑት ሴቶች ቀን ፍትህ ለማምጣት ጥረት የሚያደርገው ምክክር መደረጉ የተለየ ትርጉም አለው፡፡

ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው የታሪክ ምዕራፎች ለደረሱ ስልታዊና ግዙፍ ጥሰቶች ኃላፊነት ሊወሰድ እንደሚገባ በመገንዘብ÷ በሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጭ ማሰባሰቢያ ሁሉም ግብዓት እንዲያዋጣ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የሽግግር ፍትህ ምንነት፣ አላባዎችና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው።

በርናባስ ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.