የሀገር ውስጥ ዜና

የሩሲያ ኩባንያ ተወካዮች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎበኙ

By Shambel Mihret

March 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው የማምረት ፍላጎት ያላቸው የሩሲያ ኩባንያ ተወካዮች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎበኙ፡፡

የሩሲያ ኩባንያ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

እንዲሁም ለፋርማሲዩቲካል ሴክተር የተገነባውን የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚመለከቱ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።