Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ115 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ115 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን ያደረጉት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የጤና ሚኒስቴር ናቸው።

የተለያዩ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በቦረና ዞን የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም በመንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሳ ተሳትፈዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች የ115 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ምግብ፣ አልባሳት፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች፣ የእንስሳት መኖ ሌሎች ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.