ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በጋር እንደሚሰሩ ገለፁ
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቴስላ ኢንኮርፖሬትድ መሥራች ከኤሎን መስክ ጋር ኮቪድ19ን ለመከላከል በአፍሪካ የሚደረጉ ጥረቶችን በተመለከተ ተወያይተዋል።
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለአፍሪካ ድጋፍ ለማድረግ ኩባንያው በመነሣቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኩባንያው ጋር አብረን እንሠራለን፤ ኤሎን መስክ የፈጠራ ችሎታውን አፍሪካን ለማገልገል ሲያውል እንመለከታለን ብለዋል።
ትውልደ ደቡብ አፍሪካዊ የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪ እና የየኢንዱስትሪ ዲዛይነር ነው።
ኤሎን መስክ አሜሪካ ካሊፎሪኒያ ግዛት መቀመጫውን ያደረገው እና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የኤሌክትሪክ መኪና እና የታዳሽ ሀይል ምርቶች አምራች ኩባንያ የሆነው ቴስላ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና መስራች ነው።
ቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች በፈረንጆቹ 2019 367 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለገበያ አቅርቧል።