Fana: At a Speed of Life!

ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 112 ቢሊየን ብር መድረሱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በአሁኑ ወቅት ተቀማጭ ገንዘብ 112 ቢሊየን ብር ፤ አጠቃላይ ሀብቱ 137 ቢሊየን ብር መድረሱን ገለፀ።
ባንኩ 18ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡
በአርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና የህብረት ስራ ማህበራት አማካይነት ከዛሬ 18 አመት በፊት የተመሠረተው ባንኩ የፋይናንስ ተደራሽነቱን በማስፋት ረገድ ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት ደርቤ አስፋው፥ የደንበኞችን ቁጥርም ወደ 10 ነጥብ 4 ሚሊየን በማሳደግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆን መቻሉን ጠቁመዋል።
ባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትና የዲጂታል የባንክ አገልግሎትን በማሳደግ ረገድም ዘርፈ ብዙ ስራ ሰርቷልም ብለዋል።
በምስረታ በዓሉ ላይ የባንኩ ባለ ድርሻዎች፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ የባንኩ ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በቤተልሔም መኳንንት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.