የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታገደ

By ዮሐንስ ደርበው

March 08, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የባለ ሦስት እና አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ማሽከርከር እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከቢሮው ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በመሆኑም የአሰራር ማሻሻያው ተጠናቆ እና የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ÷ ከነገ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን ነው ቢሮው የገለጸው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!