የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተዘጋጀ ተመልካች አልባ የኪነጥበብ መድረክ በአንድነት ፓርክ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

April 11, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተዘጋጀ ተመልካች አልባ ኪነጥበባዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአንድነት ፓርክ ውስጥ እየተካሄደ ነው።

ፕሮግራሙ በብሄራዊ የሚዲያና የኪነጥበብ ግብረሃይል የተዘጋጀ ነው።

“በጥበብ በማስተዋል ይህም ይታለፋል” በሚል መሪ ቃልም ነው እየተካሄደ ያለው።

በመድረኩ ላይ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ሙዚቃዎች፣ የመድረክ ጭውውቶች፣ ግጥሞች፣ ትእይንቶች፣ የኮሚዲ ስራዎች፣ አጭር ትያትር እና የሰርከስ ዝግጅቶች ይቀርቡበታል።

በርካታ አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎችም በዚህ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡም ይሆናል።

 

በአልአዛር ታደለ