የሀገር ውስጥ ዜና

ብሔራዊ የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ ባከናወናቸው ተግባራት እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ እየተወያየ ነው

By Shambel Mihret

March 09, 2023

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት እና የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚያስችል ግምገማዊ ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ በፌደራል፣ በክልል እና በከተማ መስተዳድር የተቋቋመው የፀረ-ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ነው እየተካሄደ ያለው።

መድረኩ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የጋራ ግምገማ ለማካሄድና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በአዲሱ ሙሉነህ