Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ተጥሎ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት እግድ ተነሳ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ተጥሎ የነበረው የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት እግድ መነሳቱን የከተማዋ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ቀንአ ያደታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷የመሬትና መሬት ነክ መረጃዎችን ለማጥራት ሲባል በጊዜያዊነት ተጥሎት የነበረው የአገልግሎት እግድ ተነስቷል፡፡

እግዱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከትናንት የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መነሳቱን ነው ሃላፊው የተናገሩት፡፡

የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ባለጉዳዮችም አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ከሚመለከተው አካል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በመዲናዋ የመሬት ወረራንና ሕገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሲባል የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት ከጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት ታግዶ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.