Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።
 
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዐቢይ አበበ እንደገለፁት÷ ፕሮግራሙ በክልሉ በገጠርና ከተማ በሚገኙ 67 ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።
 
በምገባ ፕሮግራሙ በአጠቃላይ 37 ሺህ 194 ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው የገለፁት።
 
በምገባ መርሐ ግብሩም ከቅድመ መደበኛ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።
 
የምገባ ፕሮግራሙ በዋናነት ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ በአግባቡ ተገኝተው ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማስቻልና የማቋረጥ ችግርን ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
 
የምገባ ፕሮግራሙ መጀመር በተማሪዎች ዘንድ የሚስተዋለውን የትምህርት አቀባበል ውስንነት እንደሚቀርፍ መግለጸቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.