የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

March 09, 2023

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ሱዳን የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ኢስማኤል ዋይስ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ኢጋድ በቀጣናው ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተባብረው ሊሠሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።