Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ የምግብ አቅርቦቶችን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ለገሱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የምግብ አቅርቦቶችን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ለገሱ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት እያንዳንዱ ቤተሰብ አቅም ከሌላቸው ጋር “ማዕድ እንዲጋራ” ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።
 
በዚህ መሠረትም በራሳቸው በኩል ለመስተዳድሩ የምግብ አቅርቦቶችን አስረክበዋል፡፡
 
ያስረከቡት የደረቅ ምግብ ዓይነት የከተማ መስተዳድሩ ‘እጅግ ተጋላጭ እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች’ ብሎ ለለያቸው ብዙ የቤተሰብ አባል ላሏቸው 1 ሺህ ቤተሰቦች የሚበቃ ነው ተብሏል፡፡
 
በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት በይፋ የተጀመረው “ማዕድ የማጋራት” ጥሪ፣ በየ ደረጃው የሚገኙ ግለሰቦች ራሳቸው የሚመገቡትን ዓይነት ምግብ እጅግ ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ እንዲያካፍሉ የሚያነቃቃ ብሔራዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡
 
“ማዕድ የማጋራት” ጥሪ በዚህ አሳሳቢ ወቅት እጅግ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የኢኮኖሚ ጫና በተወሰኑ መልኩ እንዲያቃልል የታሳበ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.