Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የጋራ የምክክር መድረክ ነገ በመቀሌ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን የባለድርሻ እና አጋር አካላት የጋራ የምክክር መድረክ ነገ በመቀሌ ከተማ ይካሄዳል፡፡

የመድረኩ ዋና ዓላማ ከስምምነቱ በኋላ በክልሉ የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩንና በሁለቱ ወገኖች መካከል መተማመን መጎልበቱን ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምክክሩ ላይ ለመሳተፍም የብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ መቀሌ ገብተዋል።

ምክክሩ የቀድሞ ተዋጊዎችን መንግስት ዘላቂና ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥም ጭምር ያለመ ስመሆኑም ነው የተመላከተው፡፡

ይህን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማስተባበር መንግስት ሀገራዊ የትግበራ አድማስ ያለውን ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 525/2015 በማቋቋም ወደስራ ማስገባቱን ለማሳወቅ ጭምርም ነው ተብሏል፡፡

ኮሚሽኑ በማቋቋሚያ ደንቡ የተሰጡት ዓላማዎች ከተዋጊነት የሚሰናበቱ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከማህበረሰቡ ጋር በዘላቂነት እንዲቀላቀሉ እና ሰላማዊና ምርታማ ኑሮ እንዲመሩ ማስቻል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ የልማት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፉ እንዲሁም በዘላቂነት ወደ ሰላማዊ ኑሮ የሚመለሱበትን ሥርዓት መዘርጋት እና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

እንዲሁም በተቋሙ ዓላማዎች፣ ዋና ዋና ግቦች እና የባለድርሻ አካላትን ሚና በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየትና የጋራ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.