Fana: At a Speed of Life!

የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጮች ከፖለቲካ ፓርቲዎች ግብአት ለመሰብሰብ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጮችን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ግብአት ለመሰብሰብ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ እና የኢትዮጵያ ሴቶች ጥምረት ፖለተካ ፓርቲ  ሰብሳቢ ነቢያ መሀመድ÷ እንዲህ ባለ መልኩ ግብአት ተሰብስቦ ፖሊሲ ለማዘጋጀት መታሰቡ ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

የቅርቡ የሰሜኑን ግጭት ጨምሮ ያለፉ ስህተቶች፣ ግጭቶች እና የመብት ጥሰቶች ተከስተዋል ነው ያሉት።

በዚህ ሂደትም ቅጣት ሲሰጥ አለመታየቱን በመጥቀስ በዳይ ይቅር አለማለቱን ተበዳይም አለመካሱንና ፍርድ መጓደሉንም አንስተዋል።

ስለዚህም ይህ ስርዓት መስተካከል አለበት፤ ፖሊሲም መዘጋጀቱ ተገቢ ነው ብለዋል በንግግራቸው፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መብራቱ አለሙ በበኩላቸው፥ የሽግግር ፍትህ ለተጎጂዎች እውቅና የሚሠጥ፣ አመኔታ የሚያሳድግ እና የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ አስፈላጊ መሆኑን እንረዳለን ብለዋል፡፡

በመሆኑም ይህን ስርዓት በግልፅ ፖሊሲ እንዲመራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በማንሳት፥ የሽግግር ፍትህ በራሱ ግብ ባለመሆኑ ሁሉም በባለቤትነት መሳተፍ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የሽግግር ፍትህ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን የተዘጋጁ ፅሁፎችን ያቀረቡ ሲሆን ከፖለቲካ ፓርዎቹ ጋር ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሃይማኖት ወንድይራድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.