ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና መንትያ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ አመጠቀች

By Mikias Ayele

March 10, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለዳሰሳ ጥናት እና ካርታ ስራ የሚውሉ ሁለት መንትያ ሳተላይቶችን ማመጠቋን አስታውቃለች፡፡

ሳተላይቶቹ በዛሬው እለት በሰሜን ቻይና ሻንዚ ግዛት ከሚገኘው የታዩሁዋን ሳተላይት ማምጠቂያ ማዕከል ወደ ህዋ መላካቸው ነው የተገለፀው፡፡

ቲያንሁይ-6 ኤ እና ቲያንሁይ-6 ቢ የተባሉት መንትያ ሳተላይቶቹ በተሳካ ሁኔታ ወደ ምህዋር መግባታቸው ተገልጿል፡፡

ሳተላይቶቹ በዋናነት ለጂኦግራፊያዊ ካርታ ስራ፣ ለመሬት ሃብት ጥናት፣ ለሳይንሳዊ ሙከራዎች እና ለሌሎች ስራዎች እንደሚያገለግሉ ተመላክቷል።

በዛሬው እለት የመጠቁትን መንትያ ሳተላይቶች ተከትሎ የቻይና ሳተላይት ማምጠቂ የሆነው የሎንግ ማርች 465ኛ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ መፈፀሙን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡