Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የቪዛ መጠየቂያ ማዕከል በአዲስ አበባ ከፈተች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የቪዛ መጠየቂያ ማዕከል በአዲስ አበባ ከፈተች።

የቪዛ ማዕከሉ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የሁለቱን ሀገራት የቆየ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክርም ተነግሯል።

ማዕከሉ ወደ ቻይና ለሚደረግ ጉዞ በአጭር ጊዜ መረጃ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

ማዕከሉ ከፈረንጆቹ መጋቢት 13 ጀምሮ የሙከራ ጊዜ ሥራውን እንደሚጀምር ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፈረንጆቹ መጋቢት 20 ጀምሮም የቻይና ቪዛ፣ የቻይና ሆንግ ኮንግ ቪዛ ፣ የቻይና ማካዎ ቪዛ እና የመሳሰሉትን የቆንስላ ሠነድ ማመልከቻዎች እና የቆንስላ ማረጋገጫዎችን በማስተናገድ መደበኛ ሥራውን በይፋ ይጀምራል፡፡

ከላይ ለተገለጹት የቆንስላ ሠነዶች ጥያቄ አሥፈላጊው ክፍያ በማዕከሉ እንደሚፈጸምም ተጠቁሟል፡፡

አመልካቾች ፓስፖርቶቻቸውን ወይም የምስክር ወረቀቶቻቸውን ከቪዛ ማመልከቻ ማዕከሉ መውሰድ እና በሚፈልጉት ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የምክር አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡

አመልካቾች የቪዛ ማመልከቻ ቅጹን ወደ ማዕከሉ ድረ-ገፅ በመግባት መሙላት እና ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ ተብሏል።

ከላይ የተጠቀሱትን የቪዛ ጥያቄዎች ከዚህ በኋላ በማዕከሉ በኩል እንጂ ኤምባሲው በቀጥታ እደማይቀበልም ተመላክቷል፡፡

የቻይና ቪዛ መጠየቂያ ማዕከሉ በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-02 በሚገኘው ድሪም ታዎር ህንፃ ላይ ይገኛል።

በወንድሙ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.