የሀገር ውስጥ ዜና

አንቶኒ ብሊንከን በቀጣዩ ሳምንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

By Alemayehu Geremew

March 10, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

አንቶኒ ብሊንከን ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ እና ኒጀር የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የፊታችን ረቡዕ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሠላም ለማሥፈን በተወሰዱ እርምጃዎች እና የጦርነት ማቆም ስምምነቱን ተከትሎ አፈፃፀሙ ላይ እንደሚመክሩም ነው የሚጠበቀው።

በተጨማሪም የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት አጋሮችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ አካላትንም በማነጋገር የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብዓዊ መብቶች ላይም ይወያያሉ ነው የተባለው።

በተጨማሪም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።