ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ18 ሺህ በለጠ

By Tibebu Kebede

April 11, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)  በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 18 ሺህ 860  መድረሱ ተገለፀ።

ይህንም ተከትሎ አሜሪካ ከጣሊያን በላይ በርካታ ሰው በኮሮና ቫይረስ የሞተባት ሀገር በመሆን የአለም የኮሮና ወረርሽና ዋና ቦታ ሆናለች።

ሀገሪቱ በአለም በኮሮና ቫይርስ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበባት ሀገር ልትሆን የቻለቸው በኒውዮርክ በዛሬው እለት ብቻ 783 ሞት መመዝገቡን ተከትሎ መሆኑን ብሎምበርግ ዘግቧል።

አሜሪካ ቀድማ በብዛት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አለማድረጓ እና አካላዊ ፈቃቅታ በበቂ ሁኔታ ባለማድረጓ በቫይረሱ ከፍተኛ ቀጥር ያለው ህዝብ እንድታጣ እድርጓታል ተብሏል።

በተመሳሳይ በብሪታኒያኒያ በአንድ ቀን የ917 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ በሀገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 875 ደርሷል።