ከጎንደር ወደ ገንዳውኃ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ህይዎት አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጎንደር ወደ ገንዳውኃ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የአምስት ሰዎች ህይዎት አለፈ፡፡
አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከጎንደር ወደ ገንዳ ውኃ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመተማ ወረዳ በመገልበጡ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
በአደጋውም አምስት ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ሰባት ተሳፋሪዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።