የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው – አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

By Mikias Ayele

March 11, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ ተናገሩ፡፡

በዋጋ ግሽበት ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች ምርምሮች የሚቀርቡበት የምርምር ጉባዔ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄዷል፡፡

በጉባዔው የተገኙት ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ የዋጋ ግሽበት በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በሀገሪቱና በክልሉ አሉታዊ ተፅእኖዎች እያስከተለ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

የዋጋ ግሽበት እያስከተለ የሚገኘው አሉታዊ ተፅእኖዎችን ለመቀነስና ለመከላከል የረጅምና የአጭር ጊዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዋጋ ግሽበቱ መጨመር የተለያዩ መንስዔዎች መኖራቸውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ ፥ በዋጋ ግሽበት ላይ የተሰሩ የተለያዩ የምርምር ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት መደረጉን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት የወደሙትን በመገንባትና በመልሶ ማቋቋም ሂደት ፈረንሳይ እንደምትደግፍም ነው አምባሳደሩ የተናገሩት።

የኢትዮጵያና የፈረንሳይ የሁለትዮሽ ግንኙነት የተጀመረው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1897 መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።