Fana: At a Speed of Life!

በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አሰባስበው ያስረከቡ አካላት አስፈላጊውን ሰነድ በመያዝ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያክልል መንግስት በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አሰባስበው ያስረከቡ እና በማሰባሰብ ላይ ያሉ አካላት አስፈላጊውን ሰነድ በመያዝ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ክልሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት÷በአንዳንድ ዞኖች በድርቅ ምክንያት በሰውና በእንስሳት ላይ ያጋጠመውን የምግብና የውሃ እጥረት በጋራ ለመፍታት እንዲቻል የድጋፍ ጥሪ መደርጉን አንስቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ግለሰቦች፣ የግል ድርጅቶ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም መላው ህብረተሰብ አስደናቂ በሆነ መልኩ ምላሽ በመስጠጡ ክልሉ የመጀመሪያው ዙር እውቅና ሰጥቷል፡፡

አሁንም በክልሉ በድርቁ ለተጋለጡ ወገኖች በቡድንም ሆነ በተናጠል ድጋፍ የሰበሰቡም ሆነ እየሰበሰቡ የሚገኙ አካላት ገንዘቡን ለዚሁ ዓላማ ተብለው በቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ተከፍተው ይፋ በተደረጉ የሒሳብ ቁጥሮችያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ እንዲሁም በዓይነት ድጋፍ ያደረጉበትን ሰነድ በመያዝ እንደሚዘገቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምዝገባው ሳርስ አዲስ ጎማ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ዋና መስሪያ ቤት ከመጋቢት 4 እስከ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሠረት የተመዘገቡ አካላት መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት በሚደረገው 2ኛ ዙር የርክክብና የእውቅናና ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.