Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ በክልሉ ከተቋቋመው የትምህርት ጥራት አማካሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ከተቋቋመው የትምህርት ጥራት አማካሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
 
አቶ ሙስጠፌ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት÷ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ለአሁኑ እና ለቀጣዩ ትውልድ በዘርፉ መበርታት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያበረክታል፡፡
 
በ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የተገኘው ውጤት በትምህርት ዘረፉ ላይ ያለንበትን ደረጃ ያመለከተ ነው ሲሉ አጽንኦት መስጠታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በቀጣይ የኮሚቴ አባላቱ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግና በትምህርቱ ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ግንዛቤ ማሳደግ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
 
አቶ ሙስጠፌ አባላቱ በትምህርት ዘርፉ ላይ ክትትልና የመደገፍ ስራዎችን ለመስራት ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.