Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከፍተኛ ሚና አለው – ከንቲባ ከድር ጁሃር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስኬት የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ፡፡
 
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች የሰላም ጉባኤ ማጠናቀቂያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
 
በመድረኩ የተገኙት ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ በሰላም እሴት ግንባታ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ሚዛናዊ ወጣቶችን ማፍራትና ማብቃት ይኖርብናል ብለዋል።
 
ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስኬት የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም አስረድተዋል፡፡
 
በድሬዳዋ ውስጥ በባህልና ኪነ-ጥበብ፣ በፊልም፣ በሙዚቃ፣ በስፖርት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለሚንቀሳቀሱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በቀጣይ ወጣቶችን ከመደገፍ ተግባር ጎን ለጎን ተተኪዎችን ለማፍራት ጠንክረን እየሰራን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.