Fana: At a Speed of Life!

የጎርጎሮሳውያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ሀገራት ዛሬ የፋሲካ ክብረ በዓል እየተከበረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የጎርጎሮሳውያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ዛሬ የትንሣኤ በዓል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓለም ዙሪያ ያሉ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሣኤ በዓልን በተለያየ መልኩ አያከበሩ ይገኛሉ፡፡

አለም ላይ ስጋት የደቀነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደቀድሞው ለማክበር ባያስችላቸውም ዕለቱን በተለያየ የአምልኮ ስርዓቶች እያከበሩ ይገኛሉ።

ሆኖም አንዳንድ ሃገራት እንደዚህ ቀደሙ የበዓል አከባበር ስርዓት እያከበሩ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

ይህም አካሄድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲስፋፋ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.