Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ስልጠና የወጣቶችን አንድነት የሚያስተሳስር መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስልጠና የወጣቶችን አንድነት የሚያስተሳስር እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብት መሆኑ ተገለፀ፡፡

ከመጋቢት 3 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም “በወጣቶች አቅም የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል ለብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የሚሰጠው ስልጠና በባህር ዳር ተጀምሯል።

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወጣት አክሊሉ ታደሰ÷ ስልጠናው የወጣቶችን አንድነት የሚያስተሳስር እና ሀገራዊ አንድነትን የሚያጎለብት ነው ብለዋል ።

ሊጉ በቀጣይ ከተለመደው አሰራር ወጥቶ በዲጂታል አሰራር ይመራል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጎልበት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ጋሻው አወቀ በበኩላቸው ÷ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊነትን የሚያሳድግ እና ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የሚያደርግ፣የወጣቶችን ፖለቲካዊ አቅም የሚያጎለብት ነው ብለዋል።

ወጣቶች ሀገራቸውን የመጠበቅ እና የማጽናት ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል ያሉት ሃላፊው÷ ሊጉ ከመደራጀት አልፎ አደረጃጀቱ ጠንካራ ሊሆን ይገባዋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ለዚህም በዕውቀት የታነጹ ምሁራን ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባዋል ነው ያሉት፡፡

ወጣቶች ሃይልን ከሚከፋፍል አጀንዳ ወጥተው ሀገራዊ አንድነት ላይ ትኩረት በማድረግ ለጠንካራ አገረ መንግስት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጾኦ ማበርከት አለባቸውም ማለታቸውንም ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.