የሀገር ውስጥ ዜና

87 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

March 13, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 87 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ኤምባሲው ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገው፡፡

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት 87 ስደተኞች መካከል 20 የሚሆኑት በህገ ወጥ መንገድ ከየመን ወደ ጅቡቲ የገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ቀሪዎቹ 67 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ወደ የመን ለመግባት በሚያደርጉት ጉዞ በህገ ወጥ ደላላዎች እጅ ወድቀው አስከፊ እንግልት እንደደረሰባቸው ተመላክቷል፡፡