ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ቁርጠኛ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡
በደቡብ ሱዳን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ÷ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱን አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ “ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን በደቡብ ሱዳን በቆየንበት ወቅት ለእኔ እና ለልዑካን ቡድኔ ላደረጉልን አቀባበል አመሰግናለሁ” ብለዋል።
ከፕሬዚዳንት ኪር እና ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቻር ጋር ባደረጉት ውይይትም÷ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳንን መረጋጋት እና ሰላም ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ማጋራታቸውን አንስተዋል፡፡