በመዲናዋ የፍራፍሬና የሰብል ምርቶች ወደ ሸማች ማህበራት ሱቆች መግባት መጀመሩ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የፍራፍሬና የሰብል ምርቶች ወደ ሸማች ማህበራት ሱቆች መግባት ጀመሩ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም ምርቶቹን በተመጣጠነ ዋጋ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ምርቶቹ ወደ ሸማች ማህበራት በብዛት እየገቡ ያሉት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያየዘ የምርት እጥረት እንዳይፈጠርና ህብረተሰቡም በዝቅተኛ ዋጋ ማግኘት እንዲችል መሆኑም ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የሸማች ማህበር እያደረገ ያለውን የምርት ማስገባት ሂደት ተመልክተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የምርት እጥረትን ለመፍታት ከአርሶ አደሮች እየገዛ ለነዋሪዎች በተመጣጠነ ዋጋ እንደሚያቀርብ ማሳወቁ ይታወቃል።