የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፓኪስታን ባለሃብቶች ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ

By Amele Demsew

March 14, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፓኪስታን ባለሃብቶች ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።

የመግባቢያ ሥምምነቱ የፋርማሲዩቲካልስ፣ የማሸጊያ ምርቶች ፋብሪካ እና የኢንዱስትሪ ፓርክ ማሳደግ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን የተፈረመው ሥምምነት የፓኪስታን ባለሃብቶች ቡድን በኢትዮጵያ እያደረገ ያለው ጉብኝት አካል መሆኑን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

ሥምምነቱ የፓኪስታን ባለሃብቶች በቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የፋርማሲዩቲካልስ እና የማሸጊያ ምርቶች ማምረቻ ፋብሪካ እንዲገነቡ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ መንግስት የፓኪስታን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የተፈረመው የመግባቢያ ሥምምነትም በኮሚሽኑና በፓኪስታን ባለሃብቶች መካከል ዘላቂ ትብብር ለመመስረት እንደሚያስችልም ነው የገለጹት።

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!