የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬፕ ታውን ተጨማሪ በረራ ሊያደርግ ነው

By Amele Demsew

March 14, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኬፕ ታውን በሳምንት አራት ተጨማሪ በረራ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ተጨማሪ በረራውን መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀምር ነው አየር መንገዱ የገለጸው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ከኬፕ ታውን ውጪ በጆሀንስበርግ የመደበኛ በረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከ60 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት አስታውቋል።

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!